Fana: At a Speed of Life!

በቻይና በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ደቡብ ምዕራብ ዩናን ግዛት በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ የስምንት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 47 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በፍርስራሽ ስር መታፈናቸው ተገልጿል።
 
አደጋውን ተከትሎ ከ500 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ የነፍስ አድን ሰራተኞች ወደ ስፍራው መላካቸው ተጠቁሟል።
 
የቻይናው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዣንግ ጉኦኪንግ የነፍስ አድን ስራዎችን ለመምራት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ማቅናቱን ተናግረዋል።
 
አደጋው በበረዷማ ኮረብታዎች በተከበበ ገጠራማ አካባቢ የተከሰተ መሆኑ ተመላክቷል።
 
በሂማሊያ ደጋማ አካባቢ በሰንሰለታማ ተራሮች በተከበበው በዩናን ግዛት የመሬት መንሸራተት የተለመደ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን÷ የአደጋው መንስኤ ግን እስካሁን አልተገለፀም።
 
በፈረንጆቹ ጥር 2013 በግዛቱ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በትንሹ የ18 ሰዎች ህይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.