Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለከተራና ጥምቀት በዓላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በመልዕክቱ የጥምቀት በዓል በመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚከበር በዓል መሆኑን አውስቷል፡፡

በሌሎች ክፍለ ዓለማት ጭምር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ከምታከብራቸው የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱና ዓበይት በዓል መሆኑም አመልክቷል፡፡

የጥምቀት በዓል ሐይማኖታዊ ሥርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ ለዘመናት ሲከበር የመጣ በዓል እንደሆነም በመልዕክቱ ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ኢኮኖሚ ትስስር መጠናክር፣ ለሀገር ገፅታ ግንባታና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዘርፍ ዕድገት ያለው ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አብራርቷል፡፡

በዓሉ ሐይማኖታዊ ሥርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ በሠላምና በድምቀት እንዲከበር ማድረግ ለእምነቱ ተከታዮቹ ብቻ የሚተው ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያዊያን ኃላፊነት መሆኑን አንስቷል፡፡

ስለሆነም ዓሉ በሠላም እንዲከበር እና የሕዝቦች የመከባበርና ትሥሥር ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ የተጠናከረ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን በጎ ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም በሀገራዊ ፍቅርና አብሮነት ሀገራዊ አንድነታችን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እንዲጠናከር በማድረግ ረገድ ሁለም በጎ አስተዋፅዖ በማበርከት ማክበር እንዳለበት መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በዓሉ የአብሮነት፣ የሠላም፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት መገለጫ ሆኖ እንዲያልፍም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.