የባሕር በር መገኘቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚያሳድግ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን እንቅስቃሴ በእጥፍ የሚያሳድግ መሆኑ ተመላከተ፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግርም÷ የባሕር በር ለኢትዮጵያ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ረጅም ጊዜ የፈጀ እና በሳል የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውጤት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
ሥምምነቱም እንደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያለንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የኢንቨስትመንት ፍሰቱን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምር ነው ብለዋል፡፡