ኳታርና ፈረንሣይ በጋዛ ለታጋቾች መድሃኒት መላከቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኳታር እና ፈረንሣይ በጋዛ ለሚገኙ ታጋቾች መድኃኒት መላካቸው ተገልጿል።
በፈረንጆቹ ህዳር ወር ለሳምንት የቆየው የተኩስ አቁም ስምምነት ካበቃ በኋላ ኳታርና ፈረንሳይ ከእስራኤል እና የሃማስ ታጣቂ ቡድን ጋር በደረሱት ስምምነት በጋዛ ለሚገኙ ታጋቾች መድሃኒት መጓጓዝ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
መድሃኒቶቹ በግብፅ በኩል ወደ ጋዛ በማድረስ ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እንደሚቀርቡ እና ከዚያም ለሃማስ እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።
ኳታር እንደገለጸችው፤ ስምምነቱ በተከበበው የባህር ጠረፍ አካባቢ ለሚገኙ ፍልስጤማውያን ተጨማሪ መድሃኒት እና ሰብአዊ እርዳታ ማድረስንም ይጨምራል።
ስምምነቱ የተደረገው የማብቂያ ምልክት በሌለው ከ100 ቀናት በላይ በዘለቀው ግጭት ውስጥ መሆኑን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ግጭቱም በመካከለኛው ምስራቅ፣ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ደግሞ ከሰሜን ኢራቅ እስከ ቀይ ባህር እንዲሁም ከደቡብ ሊባኖስ እስከ ፓኪስታን በሚፈፀሙ ጥቃቶች ውጥረት ማንገሱ ተመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!