Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ሳተላይት ማምጠቋን ተከትሎ በታይዋን የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታይዋን ወሳኝ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከምታካሂድበት ከቀናት ቀደም ብሎ ቻይና በደቡባዊ የአየር ክልሏ ሳተላይት ማምጠቋን ተከትሎ ታይዋን የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ አስተላልፋለች።

ክስተቱን ተከትሎ በደሴቲቱ የሚኖሩ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች “ለደህንነትዎ እንዲጠነቀቁ” የሚል ፕሬዚዳንታዊ የማስጠንቀቂያ መልዕክት እንደደረሳቸው ተመላክቷል።

“የፕሬዚዳንታዊ ማስጠንቀቂያው” በታይዋን በመጪው ቅዳሜ ከሚደረገው ወሳኝ ፕሬዚዳንታዊ እና የሕግ አውጭዎች ምርጫ በፊት አንዳች ግርግር እንዳይኖር ጠቁሟል።

ታይዋንን እንደራሷ ግዛት የምትቆጥረው ቻይና በምርጫው ውስጥ ጣልቃ ገብታለች በሚል ስትከሰስ ቆይታለች።

23 ሚሊየን ህዝብ ያላትና በራሷ የምትተዳደረው ታይዋን÷ በእስያ አህጉር የበላይነትን ለመቆናጠጥ በቻይና እና አሜሪካ መካከል ላለው ፍጥጫ ቁልፍ ጉዳይ መሆኗ ይነገራል።

ምርጫው በቤጂንግ እና በዋሽንግተን መካከል ያለውን የግንኙነት አቅጣጫ ሊቀይር ይችላል ሲሉም ተንታኞች መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቻይና ሲቹዋን ግዛት ከሚገኘው የዚቻንግ ሳተላይት ጣቢያ ኢንስታይን ፕሮብ የተባለች ሳተላይት ሙሉ በሙሉ በተሳካ ሁኔታ ማምጠቋ በስፋት ተዘግቧል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.