Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በጋዛ በንጹሃን ላይ የሚደርስን ጉዳት እንድትቀንስ አሜሪካ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በጋዛ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርስን ጉዳት እንድትቀንስ አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች፡፡

የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ በጋዛ 249 ዜጎች ለህልፈት ሲዳረጉ 510 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ቢሊንከን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸውን ቀጥለው በትናንትናው ዕለት እስራኤል መግባታቸው ተገልጿል፡፡

የፍልስጤ ጤና ሚኒስቴርን ሪፖርት ተከትሎም እስራኤል በጋዛ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርስን ጉዳት እንድትቀንስ አንቶኒ ቢሊንከን በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሩ ጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማውያን መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ የሚደረገው ጫና ትክክል አለመሆኑን መናገራቸውም ይታወሳል፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ÷ በደቡብ እና ማዕከላዊ ጋዛ ላይ አዲስ ምዕራፍ ያለውን መጠነ ሰፊ ጦርነት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ጦርነቱ ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል ያለው ሚኒስቴሩ÷ ይሁን እንጂ በዚህ ተስፋ አንቆርጥም ሲል መግለጹን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በሃማስና እስራኤል መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት እስካሁን በጋዛ ከ23 ሺህ 84 በላይ ዜጎች ለሕልፈት ሲዳረጉ 58 ሺህ 926 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.