Fana: At a Speed of Life!

ለበጋው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካቶች ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጋ የበጎ ፈቃድ ጥሪያችንን በመቀበል በርካታ ልበ ቀና ባለሐብቶች እና ተቋማት ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆንም የነዋሪዎች የቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በትናንትናው ዕለት ማስጀመራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ተቋማቱ ግንባታውን በአጭር ጊዜ አጠናቀው እንደሚያስረክቡም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ከትናንትና ጀምሮ ለመዲናዋ ነዋሪዎች የተላለፉትን 389 ቤቶች በመገንባት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቲኤንቲ ኮንስትራክሽን ፒኤልሲ፣ ሀቢታት፣ ፍሊንትስቶን ሆምስ፣ የኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት፣ አቶ ሙኒር ሃይረዲን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ዶ/ር ዳንኤል፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ አቶ ቢኒያም ካሳ፣ የሰላም ፍሬ ማህበር፣ የሳይንስና ኢኖቬሽን ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ውበትና አረንጏዴ ልማት ቢሮ፣ አቶ ፋሲል ዘውዴ እንዲሁም በጋራ ሐብት በማሰባሰብ ቤቶቹን ለገነቡ ግለሰቦች እና ተቋማት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ከንቲባ አዳነች የክረምቱ ወቅት የበጎ ፈቃድ መርሐ -ግብር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁንም በማኅበራዊ ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.