Fana: At a Speed of Life!

አቡዳቢ የሩሲያ-ዩክሬንን የእስረኞች ልውውጥ እያስተባበርኩ ነው አለች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት ውስጥ ከገቡ ጀምሮ በቁጥር ትልቁ ነው የተባለለትን የእስረኞች ልውውጥ እንዲያደርጉ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እያስተባበረች እንደሆነ አስታወቀች፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ÷ በሀገራቸው አሸማጋይነት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተካሄዱት ውይይቶች ፍሬያማ ነበሩ፡፡

በሁለቱ ወገኖች በተደረሰው ሥምምነት መሠረት የተፈቱትን የእስረኞች ቁጥር ይፋ ያላደረገው መግለጫው፤ በሽምግልና ሂደቱ የሀገራቱ መንግሥታት ላሳዩት ቀና ትብብር አድናቆቱን ገልጿል።

የሽምግልናው ሂደት የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በሁለቱ ወገኖች መካከል ለዘለቀው ግጭት ሠላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው ተብሎለታል፡፡

በመሃል ንጹሐን እንዳይጎዱ ሀገራቱ ቅራኔያቸውን በውይይት እንዲፈቱ በዲፕሎማሲው ረገድ አቡዳቢ የተቻላትን ሁሉ ድጋፍ እንደምታደርግም አፅንዖት መስጠቷን አናዱሉ ዘግቧል፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.