Fana: At a Speed of Life!

ቡና አምራቾች በሚያመርቱት ልክ የሚገባቸውን ጥቅም እያገኙ እንዳልሆነ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለምናመርተው ቡና የሚገባንን ያህል ጥቅም እያገኘን አይደለም ሲሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ቡና አምራች አርሶ አደሮች ተናገሩ።

አርሶ አደሮቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ የቡና ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ችግር ገጥሞናል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን በበኩሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቡና ዋጋ ቢቀንስም በጥራት የሚመረት ቡና ግን አሁንም ተፈላጊ ነው ብሏል፡፡

በመሆኑም አርሶ አደሩ ምርቱን በጥራት እንዲያመርት የተለያዩ የግንዛቤ ሥራዎችን እየተሠሩ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻፊ ኡመር÷ ለቡና ገበያ መዳረሻነት አማራጭ የግብይት ቦታዎችን በጥናት የመለየት ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል፡፡

ከልየታው በኋላም የቡና አምራች አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበት እና ምርቶቻቸውን በራሳቸው ፍላጎት የሚሸጡበት ሁኔታ መመቻቸቱንም ነው የገለጹት፡፡

ሁለት ዓይነት የገበያ አማራጮችን በመከተልም የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ገበያ ተፈላጊነቱን እንዲጨምር ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

አርሶ አደሩ÷ የቡና ምርትን ለማሳደግ እና ተጠቃሚነቱን ከፍ ለማድረግ እያንዳንዱን ያረጀ የቡና ግንድ እንዲጎነድልና አዳዲስ ዝርያዎችን እንዲተክል የግንዛቤ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አመልክቷል።

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.