Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ “ብሪክስ”ን በዛሬው ዕለት በይፋ መቀላቀል ታሪካዊ ክስተት ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ “ብሪክስ”ን በዛሬው ዕለት በይፋ መቀላቀሏ ታሪካዊ ክስተት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት “ብሪክስ” ን በይፋ መቀላቀሏን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ነው ይሄን ያለው፡፡

ሚኒስቴሩ በጋዜጣዊ መግለጫው እንዳለው ÷ በፈረንጆቹ 2023 ነኀሤ ወር ላይ ኢትዮጵያ “ብሪክስ”ን በአባልነት እንድተቀላቀል የተደረገላትን ግብዣ በደስታ መቀበሏ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው፡፡

ግብዣውን መቀበሏ ሀገሪቷ በዓለምን ሠላም፣ ደኅንነት እና ብልጽግና በትብብር ለመሥራት ያላትን ቁርጠኝነትም ያረጋገጠ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ከዚህ ባሻገር በተለያዩ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ላይ ተሳታፊ ለመሆን ዕድል እንደሚከፍትላትም ነው የተነገረው፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በደቡብ-ደቡብ ትብብር ላይ ያላትን አስተዋፅዖ እንደሚያሳድገው ተገልጿል፡፡

በዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓት ለውጥ ውስጥ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ዕውቅና እንደተሠጠውም መግለጫው ጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ ተሳትፎዋ እንዲጎለብት የሚያግዝ ኮሚቴ እንደተዋቀረም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ከሌሎች የ“ብሪክስ” አባል ሀገራት ጋር በመሆንም በሠላምና ብልጽግና የምታደረገውን ትብብር በቁርጠኝነት እንደምትቀጥልም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.