Fana: At a Speed of Life!

የሰቆጣ ቃል ኪዳን አተገባበር ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ላይ በተሰናዳው የሰቆጣ ቃል ኪዳን አተገባበር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እየተወያዩ ነው፡፡

አዲስ አበባ በተዘጋጀው መድረክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡

የሰቆጣ ቃል ኪዳን የ2015 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2016 ዓ.ም የዕቅድ ማጽደቂያ እና የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን ማስተዋወቂያ መድረክ ነው።

በሰቆጣ ቃልኪዳን መሠረት ÷ መንግሥት ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር ዜሮ ለማድረስ እየሠራ ነው፡፡

መንግሥት ችግሩ በሥፋት በሚታይባቸውን 240 ወረዳዎች እስከ 2022 ዓ.ም ዜሮ ለማድረስ አቅዶ እየሠራ ነው፡፡

በ2014 ዓ.ም በተደረገ የተፅኖ ግምገማ ጥናት ከ59 ሺህ በላይ ሕፃናትን ከመቀንጨር መታደግ ተችሏልም ነው የተባለው፡፡

ከ2ሺህ በላይ የሚሆኑት ሕፃናትን ደግሞ ከሞት መታደግ መቻሉን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

በዘርፉ ላይ አሁን እየተተገበሩ ያሉትን ሥራዎችም ሽፋን በማሳደግ ተደራሽ የሚሆኑ ወረዳዎችን ለመጨመር እና የመቀንጨር ምጣኔውን በመቀነስ ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ልጆችን ከመቀንጨር ለመታደግ እንደሚቻል ጥናቱ ማሳየቱን የጤና ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ይህንን ሥራ ከግብ ለማድረስ የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚያስፈልግም ተነስቷል።

በበረከት ተካልኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.