ፌሊክስ ትሺሴኬዲ በኮንጎ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌሊክስ ትሺሴኬዲ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ አደረገ።
ፌሊክስ ትሺሴኬዲ የመራጮችን 70 በመቶ ይሁንታ ማግኘታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በምርጫው ውጤት መሰረት ከፌሊክስ ትሺሴኬዲ በመቀጠል ተፎካካሪያቸው የነበሩት ባለሃብቱ ሞይስ ካቱምቢ 18 በመቶ የመራጮች ድምጽ ማግኘታቸው ተነግሯል።
ሌሎቹ ተፎካካሪዎች ማርቲን ፋዩሉ አምስት በመቶ እንዲሁም ዴኒስ ሙክዌጌ ከአንድ በመቶ በታች የሆነ የመራጮችን ድምጽ ማግኘታቸው መነገሩን ዘ ዋሽንግተን ታይምስ በዘገባው አመልክቷል።