Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ድጋፉን እንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ላይ ድጋፉን እንደሚያጠናክር የኤጀንሲው የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሉዊስ አንቶኒ ሶቼት ገልጸዋል፡፡

ኤጄንሲው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸዉን ሁሉን አቀፍ የልማት ትብብሮች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከኤጀንሲው የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሉዊስ አንቶኒ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ ረዥም ጊዜን ያስቆጠረ ትብብር እንዳላቸው ያስታወሱት ሚኒስትሯ፤ ትብብሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑን ገልጸዋል።

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ላይ የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉንም አንስተዋል።

ይህ ድጋፍ በሶስት ዓመቱ የመካከለኛ ዘመን እቅድ ትግበራና በሁለተኛዉ ምዕራፍ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የትግበራ ዓመታትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሉዊስ አንቶኒ ሶቼት በበኩላቸዉ÷ የፈረንሳይ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የሚሰራቸዉን የትብብር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ኤጀንሲው በሁለተኛው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ላይም ድጋፉን እንደሚያጠናክር መግለጻቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢነርጂ በተለይም በታዳሽ ሃይል ልማት የትብብር ስራዎች መኖራቸዉን ጠቅሰው፤ በከተሞች ፕላን፣ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች ልማት፣ በግብርና ምርታማነት ማሳደግና ወጪ ንግድ ላይ በርካታ የትብብር ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.