Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ወደ ቤላሩስ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የማድረስ ስራዋን እንዳጠናቀቀች ሉካሼንኮ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ወደ ቤላሩስ የማድረስ ስራዋን ማጠናቀቋን የቤላሩስ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ተናግረዋል።
 
ሉካሼንኮ በሩሲያ ከፍተኛው የዩሬዢያ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ለመታደም በትናንትናው ዕለት በሴንት ፒተርስበርግ ተገኝተዋል፡፡
 
በወቅቱም ለጋዜጠኞች በሰጡት ምላሽ÷ ከክሬምሊን የመጨረሻው የታክቲካል የኑክሌር ጦር መሳሪያ በፈረንጆቹ 2023 ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
 
ሩሲያ ምን ያህል የጦር መሳሪያዎች ወደ ሀገራቸው እንደላከች ባይገልጹም÷ እንደ ጽህፈት ቤታቸው መረጃ ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ በቦታው ላይ እንደሚገኝ መናገራቸውን ዩ ፒ አይ ዘግቧል።
 
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር እያደረገው ባለው ጦርነት በቤላሩስ በአጭር ርቀት ላይ ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንደሚያሰፍሩ በፈረንጆቹ መጋቢት ወር ላይ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
 
በወቅቱም ቅስቀሳው በዩክሬን ያለው ግጭት ወደ ኒውክሌር ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት ለመፍጠር ነው ሲል የጦርነት ጥናት ኢንስቲትዩት መግለጹን ተከትሎ እርምጃው በምዕራባውያን ዘንድ ውግዘት እንደገጠመውም አይዘነጋም፡፡
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.