Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የጦር መርከቧ በተፈጸመበት ጥቃት መውደሙን አስታወቀች

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 16 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ አንድ የጦር መርከቧ በጥቁር ባህር በተፈጸመበት ጥቃት መውደሙን አስታወቀች።

መርከቡ ሩሲያ በምትቆጣጠረው ክሬሚያ በሚገኘው ፊዮዶሲያ ወደብ አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት መውደሙንም ነው የሩሲያ ባለስልጣናት ያስታወቁት።

የጦር መርከቡ ከተዋጊ ጀት በተተኮሰ ሚሳኤል መመታቱን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አረጋግጧል።

በክሬሚያ – የሩሲያ አስተዳዳሪ የሆኑት ሰርጌ አክሲዮኖቭ በጥቃቱ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በወደብ ከተማዋ ፊዮዶሲያ ከባድ ፍንዳታ መከሰቱን እና ስድስት ህንጻዎች መውደማቸውንም ነው የተናገሩት።

በወደብ ከተማዋ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር ተያይዞ የደረሰው ጉዳት ዝርዝር እየተጣራ መሆኑን ቢቢሲ እና አርቲ በዘገባቸው አመላክተዋል።

ቀደም ብሎ የዩክሬን አየር ኃይል በጥቁር ባህር የሩሲያን የጦር መርከብ መምታቱን ገልጾ ነበር።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.