Fana: At a Speed of Life!

ፊፋ የ2 ነጥብ 79 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የእግርኳስ ማህበር (ፊፋ) ለአባል ሀገራቱ እግር ኳስ ልማት የሚውል የ2 ነጥብ 79 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ፡፡
 
በድጋፉ በስድስቱ የአሀጉራት ኮንፌዴሬሽን ውስጥ የሚገኙ 1 ሺህ 600 በላይ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
 
የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያን ኢንፋቲኖ÷ ከእግር ኳስ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለእግር ኳስ እድገት መልሶ ለማዋል የገባነውን ቃል ፈፅመናል ብለዋል፡፡
 
በእግር ኳስ ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ሃላፊነታችን ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ፊፋ ይህን የእግር ኳስ ልማት ግልጽ በሆነ መንገድ መተግበር የሚያስችል መዋቅር አለው ብለዋል፡፡
 
ፊፋ ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2022 ድረስ 2 ነጥብ 24 ቢሊየን ዶላር ብቻ የመደበ ሲሆን በ2023 ብቻ 2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር መመደቡ ፊፋ ለዓለም እግር ኳስ ልማት ልዩ ትኩረት መስጠቱን ያሳያል ተብሏል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.