አሰልጣኝ ዘላለም ሺፈራው የሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ዘላለም ሺፈራውን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።
ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር ከተለያየ በኋላ ቡድኑን በዋናነት የሚመራ አሰልጣኝ ሲያፈላልግ የቆየው ሲዳማ ቡና፥ በመጨረሻም ከአሰልጣኝ ዘላለም ሺፈራው ጋር ሥምምነት ላይ ደርሶ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት ተረክበዋል፡፡
አሰልጣኙ ክለቡ ያለበትን የውጤት ቀውስ ይቀርፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ከ15 ቀን በኋላ በድሬዳዋ በሚደረገው 8ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡናን በመያዝ ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አሰልጣኙ ከዚህ በፊት ደቡብ ፖሊስ ፣ ደደቢት፣ አዳማ ከተማ፣ ሐዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ወልዲያ ከተማ፣ ወላይታ ዲቻ፣ ሰበታ ከተማ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝነት እና በተለያዩ የሃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡