Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ35 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሐብቶች እንዲያለሙ ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከ35 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሐብቶች መሬት ወስደው እንዲያለሙ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ውሳኔ አሳለፈ።

የአማራ ክልል የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ እንደገለጹት፥ ባለሐብቶቹ መዋዕለ-ንዋያቸውን በተመረጡ ሥምንት ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ለማፍሰስ ፈቃድ ጠይቀዋል፡፡

ባለሐብቶቹ በሆቴሎች፣ ሪዞርቶች እና ሞሎች ግንባታ እንዲሁም በጤና ተቋማት ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ መጠየቃቸው ተመላክቷል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ለ10 ሺህ 564 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሕዝብ ኢኮኖሚ የሚያነቃቃ ትላልቅ የኢንቨስትመንት አማራጭ ይዘው ለሚመጡ ባለሐብቶች ክልሉ ቀልጣፋ አገልግሎት በማቅረብ ወደ ሥራ እንዲገቡ እንደሚያግዝ ርዕሰ መሥተዳድሩ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.