Fana: At a Speed of Life!

የአሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ዲሽታ ግና በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ዲሽታ ግና በዓል እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ “ለሀገራዊ ችግሮች ሀገር በቀል መፍትሔ ” በሚል መሪ ቃል በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የ2016 ዓ.ም የአሪ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ዲሽታ ግና በዓል የብሄረሰቡን ባህል፣ እሴትና ትውፊት በሚያሳዩ አለባበስና ልዩ ልዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ደምቆ በጂንካ ሁለገብ ስታዲየም ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በብሄረሰቡ የተጣሉ ሰዎች እርቅ ሳይፈፅሙና እርቀ ሰላም ሳያወርዱ የዲሽታ ግና የዘመን መለወጫ በዓልን እንደማያከብሩ ተገልጿል፡፡

የዲሽታ ግና እሴት የሆኑት ምስጋና፣ ፍቅር፣ ዕርቀሰላም፣ አብሮነትና መረዳዳት እንዲሁም ፅዳትና ውበት የበዓሉ መገለጫ ናቸው ።

በብሄረሰቡ ዘንድ የተዘራው ሁሉ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ፍሬ የሚይዘበትና ለመሰብሰብ የሚያመቸው የታኅሳስ ወይም ሎንጋ ወር ነው ተብሎ ስለሚታመን በታኅሳስ አንድ የዘመን መለወጫ በዓል ይከበራል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.