Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለእስራዔል የአሥቸኳይ ጊዜ የመሣሪያ ሽያጭ አጸደቀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለእስራዔል የ106 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የአሥቸኳይ ጊዜ የታንክ ተተኳሽ ጥይቶች ሽያጭ ማጽደቋን አስታወቀች፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ውሳኔው የተላለፈው የአሜሪካን ብሔራዊ ደኅንነት ጥቅሞች ከማስጠበቅ አንፃር መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ተናግረዋል፡፡

እስራዔል ካለችበት መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ አንጻር ከራሷ አልፋ የቀጣናውን ሠላም እንድታረጋግጥ ውሳኔው አሥፈላጊ ነው ማለታቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ እንዲህ ያለው ወታደራዊ የመሣሪያ ሽያጭን በተመለከተ የኮንግረሱ ሥልጣን በግልጽ አለመቀመጡን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.