ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ከቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ከቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር በዱባይ ተገናኝተው ተወያይተዋለ፡፡
በውይይታቸው በሱዳን ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ በሚያስችሉ የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን መካከል የነፃ ንግድ ቀጠና ለመክፈት የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡
ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ከጉባኤው ጎን ለጎን የሱዳንን ግጭት ጨምሮ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ከሱዳን ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡