“ኮይካ” እና “ኤግዚም ባንክ” በመስኖ ልማት ዘርፍ መሳተፍ እንደሚፈልጉ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኮሪያ ዓለምአቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) እና ከኮሪያ የወጭና ገቢ (ኤግዚም) ባንክ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን የመሥኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴዔታ ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በውይይታቸውም÷ “ኮይካ” በኢትዮጵያ በመሥኖ ልማት ዘርፍ መሳተፍ እንደሚፈልግ መግለጹን ሚኒስትር ዴዔታው ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም ለሕዝቡ ተጠቃሚነት ውኃ በማጎልበት ሥራ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ማመላከቱን ነው ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገፃቸው ያስታወቁት፡፡
ኤግዚም ባንክም÷ ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት የመሥራት ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል ብለዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በኢትዮጵያ በሚካሄዱ የጥልቅ ውኃ ቁፋሮዎች እና የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የመሳተፍ ፍላጎነት አለው ነው ያሉት፡፡