Fana: At a Speed of Life!

ሕዳር 20 በቋሚነት የዓየር ኃይል ቀን ሆኖ ይከበራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዳር 20 ቀን የዓየር ኃይል ቀን ሆኖ በቋሚነት እንዲከበር መወሰኑን የዓየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አስታውቀዋል።

የዚህ ዓመት የኢፌዴሪ ዓየር ኃይል 88ኛ ዓመት ክብረ በዓልም ከሕዳር 20 ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር ቆይቶ ታኅሣሥ 6 ቀን እንደሚጠናቀቅ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አመልክተዋል።

ተቋሙ ጥናት አድርጎ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓየር ኃይል አዛዥ በኢትዮጵያ የተሾመው ሕዳር 20 ቀን 1928 ዓ.ም መሆኑን በማረጋገጥ በዚሁ ዕለት በዓሉን በቋሚነት ለማክበር መወሰኑንም ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ በለውጡ አምሥት ዓመታት ምን እንደተሰራ የምንገመግምበት እና ወደፊት ምን እንደሚሠራ የምንዘጋጅበትን መርሐ-ግብር የሚያሳዩ ልዩ ልዩ ሁነቶች ይኖራሉ ብለዋል።

በዚህ ዓመት ታኅሣሥ ሥድስት ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በዓየር ኃይሉ ሲሰለጥኑ የቆዩ ኦፊሰሮች ይመረቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።

“ጥቁር አንበሳ” የሚል ሥያሜ የተሰጠው የዓየር ላይ ትርዒት ከሌሎች ሀገራት ዓየር ኃይሎች ጋር በመሆን እንደሚካሄድም ተመላክቷል፡፡

በዓለምሰገድ አሳዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.