Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ሥምምነት ላይ ደረሰች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተመረጡ የታዳሽ ኃይል ዘርፎች ከሀገራት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የሚኒስትሮች ሥምምነት ላይ ደረሰች፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው 28ኛው የተባበሩት መንግሥታት የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ተሳትፈዋል፡፡

ኢትዮጵያን ወክለውም ሥምምነት ላይ የደረሱት ÷ ከሴራሊዮን ፣ ዚምባቡዌ ፣ ኬንያ፣ ናሚቢያ እና ሩዋንዳ ባሉበት ዴንማርክ እና ጀርመን በሚደግፉት “የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ትብብር” መድረክ ላይ ነው፡፡

በዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ “የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ትብብር” የሚኒስትሮች መድረክ ላይም ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ ያላትን የኢነርጂ ሐብት በዓይነትና በመጠን አስረድተዋል፡፡

ባለፉት ዓመታትም ከተመረተው ኃይል እስከ 1 ሺህ ጊጋ ዋት በሠዓት የሚደርስ ኃይል ወደ ጎረቤት ሀገራት እንደተላከ ገልጸዋል፡፡

“የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ትብብርም ” የኃይል ትሥሥሩን ለማሳለጥ አወንታዊ ሚና እንደሚጫወት መጠቆማቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.