Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በማስመልከት የንግድ ትርዒትና ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ሕዳር፣25፣ 2016 ( ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት የንግድ ትርዒትና ባዛር ተከፈተ።

በዓሉ ”ብዝኅነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በጅግጅጋ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው።

በዓሉን በማስመልከት የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ባህልና እሴት የሚያንጸባርቁ የተለያዩ አልባሳት የቀረቡበት የንግድ ትርዒትና ባዛር በዛሬው ዕለት ተከፍቷል።

በተጨማሪም ተኪ ምርቶች፣ የፋብሪካ እና የዕደ ጥበብ ውጤቶች እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች ለሸማቾች ቀርበዋል።

የንግድ ትርዒትና ባዛሩ በአምራቾች፣ አቅራቢዎችና ሸማቾች መካከል የንግድ ትስስርን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተገልጿል።

በመላኩ ገድፍ

መረጃዎቻችንን፦
በቴሌግራም፡- https://t.me/EthiopianNewsA
በድረገጽ፡- https://www.ena.et/
የኢዜአ ዜናዎችን በአጭር የስልክ መልዕክት ለማግኘት፡- 9111
ፈረንሳይኛ ድረ-ገጽ https://www.ena.et/web/fre
አረብኛ ድረ-ገጽ https://www.ena.et/web/ara
በአፋን ኦሮሞ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/TajaajilaOduuItoophiyaa/
በትግሪኛ ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/ethiopianewsagencytigrigna/ አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.