Fana: At a Speed of Life!

የእስራኤል ወታደራዊ ተልዕኮን ማስፋት ጋዛን የበለጠ ገሃነም ያደርጋታል ሲል ተመድ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስራኤል ወታደራዊ ተልዕኮዋን ባሰፋች ቁጥር ጋዛን የበለጠ ገሃነም ያደርጋታል ሲል አስታውቋል።
 
በጋዛ ሰርጥ የባሰ አስፈሪ ሁኔታ ሊፈጠር ነው ሲል የገለፀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዕርዳታ ሥራዎች ምላሽ መስጠት ሊከብድ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡
 
የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ካን ዮኒስ በተባለው አካባቢ በሃማስ እና በሌሎች የታጠቁ ቡድኖች ላይ ከባድ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ አመላክቷል።
 
ነዋሪዎች ከከተማዋ አንድ አምስተኛውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ የተሰጠ ሲሆን በአንድ ሌሊትም አካባቢው ከባድ የቦምብ ድብደባ እንደደረሰበት ተጠቁሟል።
 
ባለፉት ሁለት ቀናት ወደ 100 የሚደርሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች እርዳታ ወደ ጋዛ ይዘው የገቡ ቢሆንም በጦርነቱ ምክንያት አቅርቦቱ እየተስተጓጎለ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።
 
የግዛቱ ዋና የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት ሌላ ተጨማሪ ጨለማ ሌሊት ካስተናገዱ በኋላ አገልግሎቶቹ ቀስ በቀስ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ከጀመረ ወዲህ በጋዛ እስከ አሁን 6 ሺህ ህፃናትን ጨምሮ ከ15 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን በጋዛ ሃማስ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.