Fana: At a Speed of Life!

ቦይንግ 15 ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖችን ለማቅረብ የ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ውል አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቦይንግ ኩባንያ 15 ዘመናዊ የአውሮፕላን ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖችን ለአሜሪካ ዓየር ኃይል ለማቅረብ የ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ውል አሸነፈ፡፡

ኬሲ-46 ኤ ፔጋሰስ የተባሉት እነዚህ ዘመናዊ አውሮፕላኖች የዓየር ኃይሉ ጀቶች በረራ ላይ እያሉ ነዳጅ መሙላት እንደሚችሉ ዘ ዲፌንስ ፖስት አስነብቧል፡፡

የቦይንግ ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሊን ፎክስ፥ የአሁኑ ትዕዛዝ ዓየር ኃይሉ በነዳጅ ጫኝ አውሮፕላናችን አቅም ላይ ያለውን ዕምነት ያሳያል ብለዋል።

“አሁን ካለው ተለዋዋጭ ዓለም አቀፋዊ ፍላጎት ጋር በሚጣጣም መልኩ አውሮፕላኖቻችንን እንድናዘምን መነሳሳት ሆኖናልም” ነው ያሉት፡፡

የአሁኑ የአሜሪካ ዓየር ኃይል ትዕዛዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቦይንግ ለተመሳሳይ አገልግሎት የሸጣቸውን ተመሳሳይ ሞዴል ያላቸው አውሮፕላኖች ቁጥር 153 ያደርሰዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.