Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ዘመናዊ የባህር የውስጥ ለውስጥ አቋራጭ መንገድ ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ቻይና ጓንግዶንግ ግዛት የተገነባው የቻይና አዲስ የባህር ውስጥ አቋራጭ ዋሻ በዛሬው ዕለት መጠናቀቁ ተገልጿል።
ወደ 6 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ዋሻ ሼንዘንን እና ዞንግሻንን የሚያገናኘው 24 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አውራ ጎዳና አካል መሆኑ ተነግሯል።
የሼንዘን-ዞንግሻን አገናኝ መንገድ በጓንግዶንግ- ሆንግ ኮንግ- ማካኦ ታላቁ የባህር ወሽመጥ ዋና የትራንስፖርት ፕሮጀክት መሆኑ ተመላክቷል።
አንድ የውሃ ውስጥ ዋሻ፣ ሁለት ድልድይ እና ሁለት ሰው ሰራሽ ደሴቶችን ያቀፈ ሲሆን ይህም በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ፈታኝ የባህር አቋራጭ ፕሮጀክቶች አንዱ ያደርገዋል ተብሏል።
ማቋረጫው በፈረንጆቹ 2024 ለትራፊክ ክፍት እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን÷ ወደ ሥራ ሲገባ ከሼንዘን ወደ ዞንግሻን ይወስድ የነበረውን ሁለት ሰአት ወደ 20 ደቂቃ እንደሚቀንስም ተገልጿል።
የሼንዘን-ዞንግሻን አገናኝ መንገድ እንደ ሆንግ ኮንግ-ዙሃይ-ማካኦ ድልድይ ካሉ ነባር መስመሮች ጋር በመጣመር በታላቁ የባህር ወሽመጥ አካባቢ የባህር አቋራጭ እና የወንዞች መተላለፊያ አውታር እንደሚፈጥርም ነው የተመላከተው፡፡
ይህም የከተማዋን ትስስር ያሳድጋል ሲሉ የጓንግዶንግ ግዛት ኮሙኒኬሽን ቡድን ኃላፊ ዴንግ ዢዋ መናገራቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.