ንግድ ባንክ በ”ቢክ ኢትዮጵያ” የፋይናንስ አገልግሎት ውድድር አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ”ቢክ ኢትዮጵያ” የተዘጋጀውን የፋይናነስ አገልግሎት አሰጣጥ ውድድር አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለሚፈጥሩ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በሚያቀርበው የብድር አገልግሎት ውድድሩን ሊያሸንፍ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም ÷ የባንክ ተጠቃሚ ላልነበሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን በማዳረስ እና ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በተንቀሳቃሽ ንብረት ዋስትና የገንዘብ ብድር አገልግሎት በመስጠት ውድድሩን ማሸነፍ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ለዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእውቅና የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት እንደተበረከተለት ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ቢክ ኢትዮጵያ የቢክ አፍሪካ ቅርንጫፍ ሲሆን ፥ በስራ ፈጠራ ለተሰማሩ እና የስራ እድል ለሚፈጥሩ ተቋማት ክህሎትን በማጋራት አፍሪካ ከአውሮፓ ጋር የተቀላጠፈ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትስስር እንዲኖር የሚረዳ ተቋም ነው።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!