Fana: At a Speed of Life!

ፀረ-ሠላም ሃይሎች ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን በሰላም እየሠጡ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፀረ-ሠላም ሃይሎች እየተወሠደባቸው ባለው ጠንካራ እርምጃ በሠላም እጃቸውን እየሠጡ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት አስታውቋል፡፡

በቦታው ተገኝተው የሪፐብሊኩን ጥበቃ ሃይል ግዳጅ አፈፃፀም የተመለከቱት የሰሜን ሸዋ ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዲየር ጄኔራል አበባው ሠይድ እንደገለጹት÷ ጸረ ሰላም ሃይሎቹ የተሰጣቸውን የሰላም አማራጭ በመጠቀም እጃቸውን መስጠታቸው በመልካምነት የሚታይ ነው ፡፡

ኮሎኔል ግርማ ደምለው በበኩላቸው ÷ የጸረ ሰላም ሃይሎቹ የሰላም አማራጭ መከተል ለሀገርም ለክልሉም የመሠረተ ልማት እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡

በቀጠናው የተሠማራው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የህዝብና የመንግስትን ፍላጎት ለማሣካት ብሎም ዘላቂ ሠላም ለማምጣት በትጋት እየሠሩ መሆኑንም መጠቆማቸውን የመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል።

ሠራዊቱ የተሠጠውን ሀገራዊ ግዳጅ ጥንቃቄ በተሞላበት አግባብና የህዝብን ሠላም ባረጋገጠ ሁኔታ እየተወጣ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.