Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር የተኀድሶ ሥልጠና የተከታተሉ ወጣቶች ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር የተኀድሶ ሥልጠና የተከታተሉ ወጣት ጥፋተኞች ከስህተታቸው ታርመው ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀላቸው ተገለጸ፡፡

በተሳሳተ መንገድ በግጭትና ሁከት ተግባራት በመሰማራት ሕዝብና መንግስት መበደላችን ተገቢ አለመሆኑን በመገንዘብ በቀጣይ ለሠላም መሥፈን በቁርጠኝነት ለመሥራት ተዘጋጅተናል ሲሉ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ባጠፉት ጥፋትም እንደተጸጸቱ ገልጸዋል።

በቀጣይ በአካባቢው በሚከናወኑ የሠላም ማስከበር ሥራዎች በመሳተፍ ሳያውቁ በስህተት የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

በርካታ የጎንደር ከተማው ወጣቶች ለሠላም ዘብ በመቆም የተገኘውን ሠላም ወደ ተሟላ ሠላም ለማሸጋገር ከመንግሥት ጋር በመሆን ለሠላም እየሰሩ መሆኑም ተነግሯል፡፡

የተኀድሶ ሥልጠናውን የተከታተሉት ጎንደር ከተማን ጨምሮ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች በህግ ጥላ ስር የቆዩ ወጣቶች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.