Fana: At a Speed of Life!

3 ተቋማት የሕግ መዝገበ ቃላት በኦሮምኛ ቋንቋ ለማዘጋጀት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕግ መዝገበ ቃላት በኦሮምኛ ቋንቋ ለማዘጋጀት የሚያሥችል ሥምምነት በሦስት ተቋማት መካከል ተፈረመ፡፡

ሥምምነቱን የተፈራረሙት÷ የፌዴራል የፍትኅና የሕግ ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም “ጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ” መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሕግ መዝገበ ቃላቱን በሦስት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ሥምምነት ላይ መደረሱና ለሥራውም 10 ሚሊየን ብር መመደቡ ተጠቁሟል፡፡

በኦሮምኛ ቋንቋ የሕግ መዝገበ ቃላት መዘጋጀቱ÷ በፍትኅ ዘርፉ ላይ ባሉ ባለሙያዎች መካከል ከቃላት አተረጓጎምና አረዳድ ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለውን የሕግ መዛባትም ይቀርፋል ነው የተባለው፡፡

ፍትኅ ለማግኘት የሚሹ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ የኅብረተሰብ ክፍሎችም÷ ወደ ሚመለከተው ተቋም በመሄድ የሚሰጣቸውን ፍርድ በቀላሉ መረዳት የሚችሉበትን ምቹ መደላድል እንደሚፈጥርላቸው ተገልጿል፡፡

መዝገበ ቃላቱን ለማዘጋጀት በሕግ፣ በቋንቋ እና ሌሎች ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ምሁራን ይሳተፋሉ ተብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.