Fana: At a Speed of Life!

በመቀሌ የሀገራት ከተሞችን የተመለከተ የልምድ ልውውጥ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተሞች ማስፋፊያና ፕላናቸው ላይ ያተኮረ የሀገራት የልምድ ልውውጥ መድረክ በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የዩጋንዳ እና ሶማሊላንድ ከተሞች ተቋማዊና መሠረተ -ልማታዊ ማስፋፊያ ፕሮግራም ሚኒስትር ዴዔታዎች ተገኝተዋል፡፡

በመርሐ -ግብሩ የኢትዮጵያ ከንቲባዎችና የከተማ ልማት ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የልምድ ልውውጥ መድረኩን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በንግግር ከፍተውታል።

አቶ ጌታቸው የምክክር መድረኩ መቀሌ ከተማ ከጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደውና ለቀጣይ የከተማዋ መስፋፋትና መልሶ ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን በበኩላቸው፥ የልምድ ልውውጡ ከሦስቱ ሀገራት ተሞክሮዎች የሚቀመርበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ከተሞች በማስፋፊያ ፕላንና መሠረተ-ልማት ግንባታዎች ማሳያነት ለተመረጠችው መቀሌም በመልሶ ግንባታ ዋና የከተማ ልማት ስራዋ አዲስ ፍኖት የሚጀመርበት ነው ብለዋል።

ተሳታፊዎቹ በቆይታቸው የመቀሌ ከተማን የተለያዩ የመሰረተ-ልማት ገጽታዎችና የማስፋፊያ ፕላን ጉብኝት ያደርጋሉ።

በቤዛዊት ከበደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.