Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ላከሸፈችው የዩክሬን የአየር ላይ ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ መስጠቷ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን ሞስኮ ላይ የፈጸመችውን የአየር ጥቃት ሙከራ ተከትሎ ሩሲያ ለሁለት ተከታታይ ምሽት በበርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ኪዬቭ ላይ ጥቃት ማድረሷ ተሰምቷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ዩክሬን በሩሲያ መዲና ሞስኮ ላይ ጥቃት ለማድረስ የላከችው ሰው አልባ አውሮፕላን በሩሲያ ሃይሎች በጥይት ተመትቶ መውደቁን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በድሮን ጥቃት ሙከራው ምንም ጉዳት ያለመድረሱን የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጌ ሶብያኒን ተናግረዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም ሩሲያ ለሁለት ተከታታይ ምሽት በበርካታ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ኪዬቭ ላይ ጥቃት ማድረሷን የከተማዋ ወታደራዊ አስተዳደር አስታውቋል።

ይሁን እነጂ ሩሲያ በኪዬቭ ላይ የፈጸመችው የአየር ጥቃት ከባድ ጉዳት አለማድረሱን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጥቃቱን ተከትሎ በሩሲያ ከፍተኛ ዝግጅት የተደረገበትን የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ጉዳት ሳያደርስ አክሽፈዋል ያሏቸው የዩክሬን ሃይሎች አመስግነዋል፡፡

“ይህ ለዩክሬን የተከፈለ ትልቅ ዋጋ ነው” ሲሉም የሀገሪቱን የአየር ጥቃት መከላከል ሃይሎች ማድነቃቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.