Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ31 ሚሊየን ብር የቀዶ ሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 7 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ31 ሚሊየን ብር የቀዶ ሕክምና ቁሳቁስ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ድጋፍ አድርጓል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) ÷ ባለፈው ዓመት በማዕከሉ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ማዕከሉ ብቁ የሕክምና ባለሙያዎች እያሉት የቁሳቁስ እጥረት እንዳለበት መገንዘባቸውን አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ሳቢያም ማዕከሉ ከአቅም በታች እንዲሰራ መገደዱን ተረድተው ችግሩን ለመቅረፍ ቃል ገብተው እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡

በተገባው ቃል መሰረትም ባንኩ በዛሬው ዕለት ለማዕከሉ 31 ሚሊየን ብር የቀዶ ሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ድጋፉ ከ250 በላይ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችን መሥጠት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

በድጋፉ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ እና ወረፋ የሚጠብቁ ታካሚዎች እፎይታ ያገኛሉ መባሉንም የማዕከሉ መረጃ ያመለክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.