በየዓመቱ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎች ትንባሆ በማጨስ በሚመጣ ካንሰር ህይወታቸውን ያጣሉ- ጥናት
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤ ፍ ቢ ሲ) ህንድን ጨምሮ በሰባት ሀገራት ትንባሆ በማጨስ ምክንያት በሚመጣ ካንሰር በየዓመቱ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ህይወት እንደሚቀጠፍ ጥናት አመላክቷል።
የላንሴት ኢ-ክሊኒካል ሜዲሲን ጆርናል ያወጣው ጥናት እንዳረጋገጠው ህንድ፣ ቻይና፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ እና ደቡብ አፍሪካ በየዓመቱ በትንባሆ ማጨስ ከሚከሰተው የካንሰር ሞት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ።
ሲጋራ ማጨስ እና ሌሎች ሦስት መከላከል የሚቻሉ አልኮል፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና (ኤች ፒ ቪ) ማለትም በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች በድምሩ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸውንም የተመራማሪዎች ቡድን ጠቁሟል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየሁለት ደቂቃው በማህፀን በር ካንሰር የአንዲት ሴት ህይወት ያልፋል ሲልም ጥናቱ አመላክቷል።
90 በመቶ የሚሆነው ሞት የሚከሰተው ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡
ተመራማሪዎቹ እዚህ ውጤት ላይ የደረሱት በአራቱ የተጋላጭነት ምክንያቶች ዙሪያ የተደረጉ ቀደም ያሉ ዓለም አቀፍ ጥናቶችን በመሰብሰብ እና በ2020 የካንሰር ሞት ግምት ላይ ተግባራዊ የተደረጉ ግኝቶችን በመንተራስ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በየሀገራቱም በካንሰር ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ከፆታ አንፃር ልዩነት እንዳለ መግለፃቸውን ዘ ሂንዱ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!