Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ ቅመማቅመምና በርበሬ መመረቱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የቅመማቅመም እና የበርበሬ ምርት መመረቱን የክልሉ ቡናና ቅመማቅመም ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር አቶ ሬድዋን ከድር ለፋና ለብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ በክልሉ 57 ሺህ 48 ሄክታር መሬት በተለያዩ ቅመማቅመም እና በርበሬ ሰብሎች ተሸፍኗል።

ከዚህም ውስጥ ከ27 ሺህ 700 ሄክታር በላይ ያህሉ በበርበሬ ምርት የተሸፈነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

2 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የታቀደ ሲሆን እስካሁን በሩብ ዓመቱ 11 ሺህ 317 ቶን የቅመማቅመም እና የበርበሬ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን ገልጸዋል

ከዚህ በፊት ይከሰት የነበረው የበርበሬ በሽታ በስፋት መቆጣጠር በመቻሉ ምርቱ መጨመሩም ተገልጿል፡፡

በማርታ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.