Fana: At a Speed of Life!

ሞሮኮ ለመጀመያ ጊዜ በሀገር ውስጥ የተሰራውን መኪና ለሽያጭ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞሮኮ ኒኦ ሞተርስ በተባለው የሀገር ውስጥ መኪና አምራች ኩባንያ የተገጣጠመውን መኪና ለሽያጭ አቅርባለች፡፡

በተያዘው ወር ይፋ የሆነው ይህ መኪና ከደቡብ አፍሪካው ሪኖልት መኪና እና ከቻይና የመኪና ብራንዶች ጋር ይወዳደራል ነው የተባለው፡፡

መኪናው ሶስት መስኮቶች ያሉት የመንገደኞች ተሸከርካሪ ሲሆን 20 ሺህ ዶላር እንደሚያወጣም ተገልጿል፡፡

የኒዮ ሞተርስ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ናሲም ቤልካያት÷ ተሽከርካሪው የሀገር ውስጥ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ስርዓትን በመጠቀም ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ተቀርጾ የተሰራ የመጀመሪያውን ሞሮኮ ሰራሽ መኪና ነው ብለዋል፡፡

ኒዎ ሞተርስ ኩባንያ በአመት ከ3 ሺህ በላይ መኪኖችን ያመርታል ተብሏል።

በፈረንጆቹ 2017 የተመሰረተው ኒዎ ሞተርስ የሰሜን አፍሪካንዋን ሀገር ሞሮኮን የመኪና የንግድ ማዕከል ለማድረግ አላማ አለው መባሉን ብሉምበርግን ጠቅሶ አርቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.