Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከአለም ትኩረት የሚሹ በሽታዎች መድኃኒት ምርምር ኢንሸቲቭ ቡድን ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከአለም ትኩረት የሚሹ በሽታዎች መድኃኒት ምርምር ኢንሸቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሊዊስ ፒዛሮ እና ከምስራቅ አፍሪካ ቡድናቸው ጋር በሊሽማኒያሲስ ፕሮግራም ዙሪያ ተወያይተዋል።

የውስጥ እና የቆዳ ሊሽማኒያሲስ በሽታ አሁንም በተወሰኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የማህበረሰብ ጤና ችግር መሆናቸውን የጠቆሙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የውስጥ ሊሽማኒያሲስ(ካላዛር) በአመት እስከ 4ሺህ በሚሆኑ ህሙማን እና የቆዳ ሊሽማኒያሲስ እስከ 30 ሺህ በሚደርሱ ህሙማን የሚከሰት መሆኑን አብራርተዋል።

ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የህክምና ተቋማትን በማጠናከር እና መድኃኒትና የመመርመሪያ ኪት በማቅረብ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዉ ኢንሸቲቩ ለበርካታ አመታት ለፕሮግራሙ እያደረገ ላለው ድጋፍ በማመስገን በቀጣይም ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ዶ/ር ሊዊስ ፒዛሮ በበኩላቸው÷ ኢንሸቲቩ በኢትዮጵያ ከ20 አመታት በላይ በትብብር መስራን መናገራቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር ያለውን የምርምር ትብብር አሁንም አጠንክረው የሚቀጥሉ መሆኑንና ዶክተር ሊያ ባነሱት መሰረትም ከአርማዎር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት እና ከምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ጋርም በምርምር ማጠናከር ስራዎች ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸዉን አሳውቀዋል።

በውይይቱ የውስጥ ሊሽማኒያሲስ (ካላዛር) በሽታን ከኢትዮጵያ ብሎም ከአፍሪካ ለማጥፋት የበርካታ አካላት ትብብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.