Fana: At a Speed of Life!

የሕክምና ግብዓት አቅርቦት ለጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሒደት የደም ሥር ነው – ዶ/ር ሊያ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤናው ዘርፍ የሕክምና ግብዓት አቅርቦት ለጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሒደት የደም ሥር ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 5ኛውን ሀገር አቀፍ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ዓመታዊ ጉባዔ “ለዘለቄታዊ አጋርነት ለማይበገር የጤና ግብዓት አቅርቦት ስርዓት”በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ፥ በጤናው ዘርፍ የሕክምና ግብዓት አቅርቦት ለጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሒደት የደም ሥር ነው።

ለዚህም እንደ ሀገር በቁጥርም ሆነ በዓይነት እየጨመረ ለመጣው ተላላፊ ለሆኑና ላልሆኑ በሽታዎች የመድኃኒት ፍላጎት አገልግሎቱ የሕክምና ግብዓቶችን በማቅረብ ትልቁን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ የሆኑ ተግዳሮቶች ቢኖሩም በተሠሩ በርካታ የለውጥ ስራዎች በአገልግሎቱ ተጨባጭ ለውጦች መታየታችውን ነው የተናገሩት።

የግብዓቶች ምጠና ትክክለኛነትና፣ የግዥ ስርዓቱ መዘመንና በህክምና ግብዓቶች ማከማቻ መጋዘኖች መልካም ስራዎች መኖራቸውን ጠቁመው ፥ ረጅም ጊዜ ይወስድ የነበረውን የግዢ ሥርዓት እያጠረ መምጣቱን አመላክተዋል።

አገልግሎቱ አሠራሩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን አሁን ስራ ላይ ለማዋል እየተሠራ ያለውን የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀም ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የህክምና ግብዓቶች በማምረት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትጋር ተባብሮ በመስራት በመጠንም ሆነ በጥራት መድሃኒቶችን ሊያቀርቡ ይገባል ብለዋል ።

ለዚህም ከማህበራቸው ጋር በመተባበር ጤና ሚኒስቴር ለዘርፍ መጠናከር የበኩሉን ይወጣል ማለታቸውን የአገልግሎቱ መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.