Fana: At a Speed of Life!

ሄኖክ ብርሃኑ የፋና ላምሮት ምዕራፍ 15 የፍጻሜ ውድድር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠንካራ ፉክክር የታየበትና ለ9 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 15 የፍጻሜ ውድድር በሄኖክ ብርሃኑ አሸናፊነት ተጠናቅቋል ።

ውድድሩን ሃይለየሱስ እሸቱ ሁለተኛ፣ ኪሩቤል ጌታቸው ሶስተኛ እና መቅደስ ዘውዱ ደግሞ አራተኛ ሆነው አጠናቅቀዋል ፡፡

ለፋና ላምሮት ምዕራፍ 15 የፍጻሜ ውድድር ተሳታፊዎችም የአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡

በዚህ መሰረትም ውድድሩን በአንደኝነት ላጠናቀቀው ሄኖክ ብርሃኑ 400 ሺህ ብር፣ ሁለተኛ ለወጣው ሃይለየሱስ እሸቱ 300 ሺህ ብር፣ ሶስተኛ ለሆነው ኪሩቤል ጌታቸው 200 ሺህ ብር እና 4ኛ ሆና ላጠናቀቀችው መቅደስ ዘውዱ የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል።

ከቀኑ 6 ሰዓት አስከ11 ሰዓት ቆይታ ባደረገውና ከፍተኛ ፉክክር በታየበት በዛሬው የድምጻዊያን የፍጻሜ ውድድር ድምጻዊ ቴዎድሮስ ሞሲሳ በክብር እንግድነት ተጋብዞ ውድድሩን ዳኝቷል፡፡

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የማርኬቲንግ፣ሽያጭና ደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክተር ሰሎሜ አበበ÷ ውድድሩን ለዳኙ፣ በአጋርነት ለተሳተፉና ለውድድሩ ተሳታፊዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለፋና ላምሮት ምዕራፍ 15 የፍጻሜ ውድድር አሸናፊዎችም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በቀጣይ አዳዲስ አዝናኝ እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን ይዞ እንደሚቀርብ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.