Fana: At a Speed of Life!

በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሲሰለጥኑ የነበሩ ተማሪዎች ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክረምቱ መርሐ ግብር የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሲሰለጥኑ የነበሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቀዋል።

በክረምቱ መርሐ ግብር ተማሪዎች በሰውሰራሽ አስተውህሎት መመራመርና ማወቅ እንዲችሉ ሲሰለጥኑ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀጣይ ተስፋዎች እንደእናንተ ያሉ ብርቱ ተማሪዎች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት በቀጣይ ለዓለም ብሎም ለሀገር አስፈላጊው ቴክኖሎጂ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያን ግብርናና ሌሎችንም መስኮች የተሻለ ለማድረግ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ በበጎ ጎኑ ሰውን ሊጠቅም በሚችልበት ሁኔታ በትኩረት ልትሰሩ ይገባል ሲሉም ለተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት መርሃ-ግብር የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ስልጠናን ሲከታተሉ የነበሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪውዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

የፕሮግራሙ አላማ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የሰው ሰራሽ አስተውህሎት እውቀትና ክህሎት ማዳበርና ማበረታታን ያለመ ነው።

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.