Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከመንግስት ሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

ውይይቱን የከፈቱት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ መካሻ ዓለማየሁ ÷ የገጠመንን የፀጥታ ችግር ለማስተካከል በተሠሩ ሥራዎች አንፃራዊ ሠላም ተገኝቷል ብለዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ በተፈጠረው የሠላም እጦት ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች መድረሱን አስታውሰዋል፡፡

አሁን የተገኘውን አንፃራዊ ሠላምም ዘለቂ ለማድረግ የመንግሥት ሠራተኛው ቁልፍ ሚና መጫወት እንዳለበት አንስተዋል፡፡

የውይይት መድረኩ ዋና ዓላማም ለሠላም የመንግሥት መዋቅሩን በተሟላ አቅም ወደ ሥራ ማስገባትን መሆኑን የአማራ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች በመንግት በትኩረት ተይዘው እየተሠራባቸው መሆናቸውን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው ÷ሁላችንም ግጭቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች ታቅበን በልማትና በመልካም አሥተዳደር ሥራዎቻችን ላይ ማተኮር ይገባናል በማለት አሳስበዋል።

የኮማንዶና አየር ወለድ ምክትል አዛዥ እና የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል አበባው ሰይድ በበኩላቸው ÷ ከሠላም እጦት የሚገኝ ትርፍ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ሠራተኛው ለሠላም መስፈን በአንክሮ እንዲሠራም አሳስበዋል።

የመንግስት ሠራተኞች በበኩላቸው ÷ ከሠላም ዕጦት የሚገኝ ትርፍ ስለሌለ በማኅበራዊ ትሥሥር ገፆች ከሚነዙ ሐሰተኛ መረጃዎችና አሉባልታ በመራቅና የሚጠበቅብንን ተቋማዊ ተግባር እናከናውናለን ፤ ለሠላም መስፈንም የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.