Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት ከአፍሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻል አለበት – የቼክ ጠቅላይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት ከአፍሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻል እንዳለበት የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ አስገነዘቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ፊያላ የአውሮፓ ሀገራት ከአፍሪካ ጋር ላላቸው ትብብር እምብዛም ቦታ አልሰጡትም ሲሉ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የአውሮፓ ሀገራት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት እየፈተሹና እንደሆነ ጠቅሰው፤ ለአፍሪካ ጉዳይ ቦታ እንየሰጡና ከዚህ በፊት የነበራቸውን አካሄድ በማረም ያላቸውን ግንኙነት ለማሻሻል እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ፒተር ፊያላ ዕለተ አርብ ወደ አፍሪካ አኅጉር አቅንተዋል ፤ በኢትዮጵያም ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ፒተር ፊያላ ወደ አፍሪካ አኅጉር ከማቅናታቸው በፊት በኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ለመወያየት ማቀዳቸውን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ ቼክ ሪፐብሊክ ለአፍሪካ ሩቅ እንደሆነች ማሰብ ማቆም አለባት ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና አይቮሪ ኮስት በማቅናት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እየሞከሩ እንዳለ ዩራክቲቭ አስነብቧል፡፡

ሩሲያና ቻይና ከአፍሪካ አኅጉር ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው አስረድተው፤ አውሮፓም የነሱን ፈለግ በመከተል ግንኙነቷን ብታጠናክር አትራፊ እንደምትሆን አመላክተዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ ÷ ቼክ ሪፐብሊክም ሆነች የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ችላ ማለት የለባቸውም፡፡

ከፖለቲካዊ ግንኙነት ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውንም ለማጠናከር መሥራት እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ ቼክ ሪፐብሊክ ከአፍሪካ ጋር በገቢና ወጪ ንግድ ለመተሳሰርና አጋሮቿን ለማስፋፋት እየጣረች እንደምትገኝ መጠቆማቸውን ዩሮአክቲቭ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.