Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በአዎንታ ሊመለከቱት ይገባል-ላውረንስ ፍሪማን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በአዎንታዊ መልኩ ሊያዩት እንደሚገባ አሜሪካዊው የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተንታኝ ላውረንስ ፍሪማን ገለጹ።

አሜሪካዊው የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተንታኝ ላውረንስ ፍሪማን እንደገለጹት ÷የኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚነት ጥያቄ ህጋዊና ፍትሃዊነትን እንዲሁም በጋራ መልማትን መሰረት ያደረገ ነው ።

በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ለሆነችው ሀገር የወጪና ገቢ ንግድ እድገት ብቻ በማሰብ የተነሳ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣናው አገራት ልማትን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በሮችን የመጠቀም ፍላጎትና መሻት ተገቢነት ያለውና የአፍሪካ ቀንድ ሕዝብ የኢኮኖሚ እድገትን ለመጨመር አስተዋጽኦ አለው ሲሉም ገልጸዋል ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ።

በመሆኑም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በአዎንታዊ መልኩ መገንዘብ አለባቸው ሲሉም ነው የተናገሩት።

በባህር በር ብቻ ላይ ሳይገደብ በምስራቅ አፍሪካ ያሉ በርካታ ወደቦችን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ እድገት አካሄድን ተከትሎ መጠቀም የሚቻልበትን ሁኔታም ከግምት ያስገባ ምክክር ቢያደርጉ መልካም መሆኑንም ጠቁመዋል።

የባህር በር አማራጭና ወደቦች አጠቃቀም ላይ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ተነጋግረው የመፍትሔ ሀሳቦችን ማፍለቅ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.