ኢትዮጵያና አሜሪካ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2016፣ (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና አምባሳደሩ በአሜሪካ ለሁለት ሳምንታት የአመራርነት ሥልጠና ወስደው የተመለሱ 25 የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ም/ፕሬዚዳንቶች ጋር ስለነበራቸው ቆይታ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያና አሜሪካ ከፈርንጆቹ 1950 ዎቹ ጀምሮ በትምህርት ዘርፍ በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡