በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች የልማት ሥራዎች ጉብኝት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ በአርሲ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ እና ሌሎች ዞኖች የልማት ሥራዎች እየተጎበኙ ነው፡፡
በጉብኝት መርሐ ግብሩ ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች እና ሴቶችን ጨምሮ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡
የጉብኝት ተሳታፊዎች በዞኖቹ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በዚህም የመንገድ ፕሮጀክቶች፣ የግብርና ሥራዎች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች እንዲሁም የዶሮ፣ የወትተ፣ የከብት ማድለብ እና የንብ ማነብ ሥራዎች መጎብኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡