Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የስታርትአፕ ሽልማት በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የስታርትአፕ ሽልማት የአፍሪካ ጉባኤ ከጥቅምት 14 እስከ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ይካሄዳል፡፡

ጉባኤውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት እና ከግሎባል ኢኖቬሽን ኢኒሼቲቭ ግሩፕ ጋር በመተባበር እንደሚያዘጋጁት ተገልጿል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እንዳሉት÷ ጉባኤው ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን አቅም የምታሳይበት ይሆናል።

በተጨማሪም÷ በዘርፉ ያለውን አቅም ለማሳደግ እንደሚያስችልና ለስራ ፈጠራ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም ተናግረዋል፡፡

ጉባኤው በኢትዮጵያ ለስታርትአፕ፣ ለጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች እና ኢንተርፕሪነሮች ምቹ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር ትልቅ
ፋይዳ ይኖረዋልም ነው የተባለው፡፡

በመድረኩ ከ80 በላይ ስታርታትአፕና ሥራ ፈጣሪዎች የሚገኙ ሲሆን ለአሸናፊዎች ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በመሰል ውድድሮች አሸናፊ የሆኑና ችግር ፈቺ የስራ ፈጠራ ያቀረቡ 400 የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ስራቸውን የሚያሻሽሉበትና ወደ ምርት የሚገቡበት ሁኔታ እንደተመቻቸላቸው ሚኒስትሯ አስታውሰዋል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.