Fana: At a Speed of Life!

በተከለከሉ መንገዶች ላይ ሲንቀሳቀሱ በተገኙ 687 ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተከለከሉ መንገዶች ላይ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 687 ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ተሽከርካሪዎች በመዲናዋ 5 የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በስራ መግቢያ እና ከስራ መውጫ ሰዓት ለብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት በተለዩ መንገዶች ላይ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ነው ተብሏል፡፡

የኤጀንሲው የመንገድ ደህንነት የግንዛቤ ዳይሬክተር ብርሃኑ ኩማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት እንዳይንቀሳቀሱ በመመሪያ የሰዓት ገደብ የተጣለባቸው የከባድ ተሽከርካሪዎች ላይም ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.