Fana: At a Speed of Life!

በልማት ሴፍቲኔት የወጣቶች ፈጠራ ፕሮጀክት 400 ወጣቶችን በሙከራ ትግበራ ለማሳተፍ ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በፌዴራል የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የልማት ሴፍቲኔት የወጣቶች የስራ ፈጠራ ፕሮጀክት 400 ወጣቶችን በሙከራ ትግበራው ለማሳተፍ ዝግጅት እየተደረገ  መሆኑ ተገለጸ።

በፕሮጀክቱ  ሽፋን ለመስጠት በዕቅድ ከተያዙት 100ሺ ወጣቶች መካካል በ400 ወጣቶች ላይ የሙከራ ትግበራ ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

በኤጀንሲው የከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ዋና አስተባባሪ አቶ ደበበ ባሩድ ÷ፕሮጀክቱን ለመተግበር 500ሺ ዶላር የተመደ ሲሆን ተግባራዊ ለማድረግ የሚስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችም እየተፋጠኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አስተባባሪው አያይዘውም ፕሮጀክቱ የሚጀመረው በቅርቡ የከተሞች ሴፍቲኔት ስቲሪንግ ኮሚቴ የከተማ ልማት ሴፍቲኔት ፕሮግራሙ ያስመዘገበውን የአፈፃፀም ውጤታማነት በመገምገም የወጣቶች የስራ ፈጠራ ፕሮጀክት በአዲስ መልክ ተካትቶ እንዲተገበር ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ነው ብለዋል፡፡

በ400 ወጣቶች ላይ በፓይለት ፕሮጀክት የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ጋር በጋራ በመሆን የሚከናወን ሲሆን በትምህርት ደረጃቸው ከ8 እስከ 12ኛ ድረስ ባለው ሂደት ትምህርታቸውን ያላጠናቀቁና ያቋረጡ ወጣቶችን የሥራ ባለቤት ለማድረግ የተነደፈው  ነው ተብሏል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ከሌሎች አገሮች ልምድ በመውሰድ የተቀመረ መሆኑንም የገለፁት አስተባባሪው ወጣቶቹን በኢንዱስትሪው ውስጥ በስልጠና እንዲበቁና የራሳቸውንም የስራ መስክ እንዲከፍቱ እንዲያስችል ተደርጎ የተቀረፀ  ነውም ነው ያሉት

ከዚያ ባለፈም በዚህ ፕሮጀክት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ጉልህ ሚና እንዲጫወቱም እየተሰራ ነው ማለታቸውን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.